top of page
Tour Eiffel en soirée

​የአማራ ማህበር በፈረንሳይ

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ​

Black Green Simple Beauty Daily Vlogger Facebook Cover.jpg

የአማራ ማህበር በፈረንሳይ ድርጅታዊ መዋቅር 

Vert et Blanc Gouvernement Post Twitter Publication Twitter (2).jpg
R.jpg
landing-115-1.png

የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

የአማካሪ ቦርድ

የዲስፕሊን እና ቁጥጥር ኮሚቴ

መረጃ

የአማራ ማህበር በፈረንሳይ ዓላማ

በማህበሩ የሚከናወኑ የበጎ አድራጎት ተግባራት

1) በኢትዮጵያ እጅግ ኋላ በቀሩ እና በተመረጡ የአማራ ወረዳዎች የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ከሚከናውኑ
ግብረ ስናይ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት ለተማሪዎች የመማርያ ግብአት የሚሆኑ ቁሳቁስን ከህዝብ በማሰባሰብ ለተረጂዎች
ማድረስ ...
2) በኢትዮጵያ በአማራ ወረዳዎች በተለያዩ ምክንያት ወላጆቻቸውን አጥተው ያላሳዳጊ የቀሩ ልጆችን በበጎ ፈቃድ ሞግዚት
ሆነው ሊረዱ የሚችሉ ግለሰቦችን በ ፈረንሳይ በማፈላለግ ደጋፊ እንዲሆኑዋቸው ማገናኘት።
3) በኢትዮጵያ አማራ አስተዳደር ለተመሰረቱ የ ሰርከስ ክበቦች የአቅም ግንባታ የሚውል የሰርከስ ግብአቶች ከፈረንሳይ
በጎ አድራጊዎች በማሰባሰ እንዲሁም ከ ፈረንሳይ ባለሙያዎች ድጋፍ የሚያገኙበት ጥረት ማድረግ።
4) የጥገኝነት ጥያቄ ለማቅረብ ፈረንሳይ የገቡ ኢትዮጵያዊ የአማራ ልጆችን በቋንቋቸው ጉዳያቸውን ለማስረዳት ይችሉ
ዘንድ እንዲሁም ከፈረንሳይ አኗኗር ዘዴ ጋር ይላመዱ ዘንድ የምክር አገልግሎት
መስጠት ጉዳያቸው ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ መርዳት እና አማርኛ የማስተርጎም አገልግሎት መስጠት።
5) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የሆነውን አማርኛ ለ ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ፈረንሳይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን ታዳጊ ህፃናት
እንዲሁም ቋንቋውን ለማወቅ ለሚፈልጉ ፈርንሳዊያን ድጋፍ ማድረግ በረጅም እቅድ በፓሪስ አንድ የቋንቋ ማስተማርያ
ማእከል መክፈት።
6) ከኢትዮጵያ ውብ የሆነ የአማራውን ባህላዊ ውዝዋዜ እና ዜማ የሚጫወቱ አርቲስቶችን በፈረንሳይ በመጋበዝ የባህል
ልውውጥ እና የሙዚቃ ምሽቶችን ማዘጋጀት።
7) በኢትዮጵያ የአማራ አስተዳደር ድንቅ የቱሪስት መስብ የሆኑ ቦታዎችን በፈረንሳይ ህዝብ ይታወቁ ዘንድ ኢግዚብሽን
ማዘጋጀት ፣ የባህላዊ አልብልሳት ኤክስፓ ማዘጋጀት፤ አስተዋዋቂ በራሪ ብሮቸሮች መበተን እና የቱሪዝም መረጃ ማድረስ።
(8) በአለፈት ዘመናት በኢትዮጵያና በፈረንሳይ ሕዝብ እንዲሁም በአማራ ማህበረሰብ የነበረውን የባህል ትስስር ይበልጥ
በማጎልበት በሁለቱ ህዝቦች ዘንድ የቆየውን የህዝባዊ ትስስር ይበልጡን በማጠናከር ወዳጅነትን እንዲጎለብት ማድረግ
9) (2) በረጅም እና በአጭር ጊዜ እቅድ በአማራው ላይ የሚደርሰውን ችግር ለማስቀረት በኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ
ለሆኑ ወላጅ አልባ ህፃናት የትምህርት እድል እንዲያገኙ ማድረግና ለመቋቋያ የሚሆን ግብአት በማቅረብ ከሚደረስባቸው
የስነልቦናዊ ጥቃት መታደግና ፍቅር አግኝተው በእንክብካቤ እንዲድጉ ወንድማዊ እገዛ መስጠት
10)(3) በኢትዮጵያ በአማራው ህብረተሰብ ዘንድ የሚስተዋሉ አላስፈላጊ ጎጂ ባህሎችን ለማስቀረት መስራት ለምሳሌ
እንደ የሴት ልጅ ግርዛት ፥ ያለ እድሜ ጋብቻ፣ የአሥገድዶ መደፈር ፤ የሴቶችን የእኩልነት መብት መከበር በአንዳንድ
አላስፈላጊ ምክኒያቶች ከህብረተሰቡ ለሚገለሉ ማህበረሰቦች ከዚህ ተፅኖ እንዲወጡ ማድረግ፥ በሴቶች ላይ የሚደረሱ
ፆታዊ ትኮሳዎች እንዲቀየሩ ለህብረተሰብ ትምህርት መስጠት

Black Green Simple Beauty Daily Vlogger Facebook Cover.jpg

አባልነት


 በግል የማህበሩ አባል ለመሆን ፦

  • ማንኛውም በትወልድ ሐረጉ ዐማራ የሆ/ነች እድሜው/ዋ 18 እና ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች የድርጅቱን ዓላማ፣ ተግባርና

ህገ ደንብ ሙሉ በሙሉ ዮተቀበለ/ች በድርጅቱ ውስጥ በአባልነት መሳተፍ ይችላል/ትችላለች፤

  • ማንኛውም አባል በዐማራው ነገድ ላይ የተቃጣውና እየደረሰ ያለውን መጠነ ሠፊ ግፍና የጥፋት ዘመቻ በራሱ ወገንና ማንነት

ላይ የተቃጣ እኩይ ተልዕኮ መሆኑን የሚያምንና ይህንንም መካከል ዐማራው በሚያደርገው መራራ ህልውና አደጋ የመጠበቅና
የመከላከል፣ ብሎም ህዝባዊ የመከላከል ሰባዓዊ ዲሞከራሲያዊ፣ሃገራዊ የባለድርሻ ተጋሪነት መብቱ ለማስከበር በሚያደርገው
ሁለገብ ትግል ጉልህ አስተዋጽኦ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ/ች፣

  • ማንኛውም የማህበሩን ዓላማና ተግባር ሙሉ ለሙሉ የተቀበለ በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ መንገድ ማህበሩን የሚጻረር፣

አልያም ፀረ- ዐማራ አቋም የሚያራምድ ድርጅት ወስጥ የማይሳተፍ፣ በፈረንሳይ መንግስት ህግ መሠረት ህገወጥ ተብለው በተፈረጁ
ከባድ የወንጀል ተግባራት ውስጥ ያልተሳተፈ የድርጅቱ ሙሉ አባል መሆን ይችላል/ትችላለች፤
የማህበሩንም ሆነ የዐማራውን ዕድገትና ልማት ለማረጋገጥ በሚደረግ ማንኛውም ሁለገብ ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ ለማድረግ
ሙሉ ፍቃደኛ የሆነች፣

  • ማንኛወም በማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ በተደነገገው መሠረት የአባልነት ቅጽ የሞላ/ች እንዲሁም የአባልነት ክፍያውን

በየወቅቱ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች የድርጅቱ ሙሉ አባል መሆን ይችላል/ትችላለች፤

  • ማንኛውም አባል በቅድሚያ የአባልነት ጥያቄ ሲያቀርብ የድርጅቱን ዓማና ተግባር እንዲሁም ህገ-ደንብ በፅሁፍ የሚቀርብለት

ሲሆን፤ ይህንኑ አምኖበት መቀበሉንና መስማማቱን በአባልነት ቅፁ ላይ በፊርማው ሲያረጋግጥ በዓላማም በአካልም ድርጅቱን
እንደተቀላቀለ ይወሰዳል፤

  • ማንኛዉም አባል በቅድሚያ የአባልነት ጥያቄ አቅርቦ ማመልከቻው በስራ አመራር ታይቶ በአንድ ወር ጊዜ ውሳኔ የሚያገኝ

ሲሆን፣ ነገር ግን ማመልከቻውን ስራ አመራሩ ካላመነበት ለመቀበል የማይገደድ ሲሆን ምክንያቱን የማሳወቅ ግዴታም የለበትም፣

​የማህበሩ ግብ(ራዕይ) ፦

 

  • ዐማራው ብሔራዊ ህልውናውን፣ታሪካዊ አንድነቱንና የማንነት ክብሩን አስጠብቆ፣ ህዝባዊ ልዕልናውንና ሃገራዊ ባለድርሻነቱን

አረጋግጦ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ የዜግነት መብቱን እኩል አስከበሮ፣ባስተማማኝ ዘላቂ ሰላምና ማህበራዊ ደህንነቱና እድገቱ
አስጠብቆ እንዲኖር ማድረግ፣

  • ጠንካራ ህዝባዊ መሠረት ያለው ሁለገብ የወል ህጋዊ የሲቪክና የልማት ተራድኦ ተቋም (ማህበር) ገንብቶ፣በዘመናዊ፣

ሳይንሳዊ ጥበብ የተመራ፣ በኢኮኖሚ እድገት የዳበረ፣ ባህሉን፣ እምነቱን፣ ቅርሱንና ውርሱን የጠበቀ፣ ሞራሉ የተገነባ፣ በጤናማ አስተሳሰብና በመልካም ስነ-ምግባር የታገዘ፣ መብቱንና ግዴታውን ለይቶ የሚያውቅ፣ የሚያከብርና የሚያስከብር ጠንካራ ህብረተሰብ ተገንብቶ ማየት፣

  • 1ችግሮቹን በራሱ የመፍታት ብቃትና አቅም ያለው፣ የዐማራውን መብትና ጥቅም ሃገራዊ ባለድርሻነት ለማስከበር በቁርጠኝነት

የቆመ፣ በራሱ የሚተማመን፣ ሁለንተና እድገቱ የተጠበቀ፣ ዓለም አቀፍ አስተሳሰቡ ያዳበረ፣ ምንግዜም ለማንነቱ፣ ለክብሩና ለነፃነቱ
ዘብ የቆመ፣ ለወገኑ አለኝታን መከታ የሆነ ማህበረሰብ በሃገር ውስጥና በውጭ ተገብቶ ማየት፣

  • ተመሳሳይ ዓላማ የሚያራምዱ አቻ ማህበራት፣ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር ተባብሮና ተቀናጅቶ የሚሰራ፣ ዐማራነትን፣ ነፃነትንና ኢትዮጵያዊነትን አጣምሮ የያዘ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ የልማትና የዕድገት ተቋም መገንባት፣ ብሎም በፈረንሳይ የማህበረሰብ ህግ አግባብ መሰረት ከዚሁ ዓላማና ተግባር የሚረዳ ማንኛውንም የልማት ተራድኦና ፈንድ የሚያስተባብር ብቃት ያለው ህጋዊ አካል መገንባትና በመላው አውሮፓ አርዓያነት ያለው ሥራ እንዲሠራ ማስቻል ነው።

NOUS CONTACTER

66 Avenue des Champs-Élysées, Paris, France

​+33753086029

Merci pour votre envoi !

Subscribe Form

Thanks for subscribing!

bottom of page